Com Hahu
Com Hahu
Level 1 reviewer
number of reviews(3)
number of helpful votes(3)

member since: 14-12-2015

የኣርታኢዎች ድጋፍ እና ግብኣት ኣሰጣጥ አለ ?

Broadcasted by: Ethiopia Broadcasting Corporation
በቅድሚያ አየር ላይ የዋለው ዋናውን ዘገባ ያንብቡ
ኢቢሲ 13 / 07 / 2009
*** የ2፡ዐዐ ቢዝነስ ዘገባ በቴሌቪዥን

የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ኘሮጀክት ግንባታ 9ዐ % መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት አስታወቀ፡፡ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም የዲፖው የማከማቸት ዓቅሙን በ3ዐ ሚሊዮን ሊትር ያሳድጋል፡፡ ስብሃት ግርማ
የሃገሪቱን የነዳጅ ፍላጎት በማጥናት የተጣራ የነዳጅ ምርት ወደ ሃገሪቱ ማስገባት እና ሃገሪቱ የሚያስፈልጋት የመጠባበቂያ ነዳጅ ማከማቸትም ዓላማው አድርጎ የተቋቋመ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በተለያዩ ምክንያቶች የነዳጅ መስተጓጎል እና መቋረጥ እዳይከሰት የክምችት መጠኑን እያሳደገ ይገኛል፡፡
በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች 13 ስትራተጂክ የነዳጅ ዲፖዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል፡፡ በዲፖዎቹ ጠቅላላ መጠባበቂያ ነዳጅ የማጠራቀም ዓቅምም 367ሺ ኪዩቢክ ሜትር ደርሷል፡፡ ይህም የአገሪቱን የ45 ቀን የነዳጅ ፍጆታ የሚሸፍን ነው፡፡ ይህንን የነዳጅ ፍላጎት እና የማከማቸት ዓቅም ይበልጥ ለማሳደግም በዚህ የአዋሽ ዲፖ የማስፋፊያ ኘሮጀክት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
” የአዋሽ ዲፖ ማስፋፊያ ኘሮጀክት በዋነኝነት የሚሰሩለት ነዳጅ የመጫን ፣ የማራገፍ፣ በአጠቃላይ ሪዘርቭ ክምችት የመያዝ ዓቅም ነው፡፡ ምንድነው ሪዘርቭ የመያዝ ዓቅሙ ወደ 3ዐ ሚልዮን ሊትር ነው፡፡ የመጫን ዓቅሙ በሰዓት 16 መኪና ነው፡፡ የማራገፍ ዓቅሙ በሰዓት 6 መኪና ነው፡፡ ይህ ኘሮጀክት መኪኖች ከመጫን እና ማራገፍ ባሻገር የባቡሮቹም የመጫን እና የማራገፍ ስራ የመስራት እያዘጋጀን ነው፡፡ አዋሽ እንደምታወቁት ማዕከላዊ ቦታ የሚገኝ ዲፖ ነው፡፡ በተለይ ለአብዛኛው ለደቡብ ለምስራቅም እንደዚሁም ለማዕከላዊም ለምዕራብም ሊያደርስ የሚችል ዲፖ ስለሆነ በጣም ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው፡፡ ለወደፊቱም የፖይኘ ላይኑ ትራንስፖርትም ሲጀመር ወደ እዚህ ዲፖ የሚመጣው እና አቪንቹዋሊ አዋሽ ዲፖ ጅቡቲም የሚተካ ሊሆን ነው፡፡
በ1992 1ዐዐ ሚሊየን ሊትር ቤንዚን ነጭ ናፍጣ እና ከሮሲን የነዳጅ ዓይነቶች በማከማቸት ስራውን የጀመረው የነዳጅ ዲፖ ግንባታው 9ዐ በመቶ ተጠናቋል፡፡ የማከማቸት ዓቅሙ ከማሳደግ ባለፈ በጅቡቲ ወደብ ላይ የሚፈጠረው መጉላላት በማስቀረት ጊዜን እና ወጪን እንደሚቀንስ ታምኖበታል፡፡
አሁን ባቡሩን ተግባራዊ ስናደርግ በአንድ ሎኮሞቲቭ እስከ 36 ፍርጎዎች መጎተት እንደሚችል መረጃ ሰጥተውናል፡፡ ያ ማለት አንዳንድ ለኮሞቲቭ 7ዐ መኪናዎችን ይተካል ማለት ነው፡፡ ወደ ግንቦት አጋማሽ አከባቢ ይጠናቀቃል ብለን እንጠብቃለን ፡፡
እንደ አለም ኢነርጂ ኤጀንሲ መስፈርት አንድ አገር ቢያንስ የ9ዐ ቀን ፍጆታን የሚሸፍን የመጠባበቅያ ነዳጅ ሊኖራት እንደሚገባ ያመለክታል፡፡ አገሪቱም ያላትን የ45 ቀናት የነዳጅ ክምችት ይበልጥ ለማሳደግ አዋሽ እና ዱከምን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ ዲፖዎችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡

“የኣርታኢዎች ድጋፍ እና ግብኣት ኣሰጣጥ አለ ? ”

በአሁኑ ሰዓት በየሚዲያ ተቋማቱ ጋዜጠኞች ዜና ይዘግባሉ ፡፡ የሚዘግቡት ዘገባ ግን የጋዜጠኝነት ሚናቸውን ከመወጣት ይልቅ የህዝብ ግንኙነት ሙያን ተክተው ሲሰሩ ያሳያል፡፡ይህንን ዓይነቱ የኣዘጋገብ ችግር በኣብዛኛው በጀማሪ ጋዜጠኞች ጎልቶ ይታያል፡፡ ሆኖም ልምድ ባካበቱ ኣርታአዎች/ Editors/ እጅ ላይ ሲደርስ የመታረም ዕድሉ ከፍተኛ ነበር፡፡
ነገር ግን ይህ ዓይነቱ አዘጋገብ በተዋረድ ያሉትን ኣርታኢዎች ኣልፎ አየር ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ ይህም
የኣርታኢዎች ድጋፍ እና ግብኣት ኣሰጣጥ እንድንነጋገርበት ይጋብዛል፡፡
አስረጅ፡- እላይ የተጠቀሰው የዜና መሪ ዓንቀፅ የሚነግረን የሚከተሉትን ፍሬ ነገሮች ነው፡፡
• የአዋሽ ዲፖ ማስፋፊያ ግንባታ ኘሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው
• መጠናቀቂያው በመቶኛ ሊሰላ 9ዐ ላይ ደርሷል
• ዲፖው ሊጠናቀቅም የመጠባበቂያ ነዳጅ የማከማቸት ዓቅም ያሳድጋል
• በሊትር የተሰላ የማከማቸት ዓቅም ዕድገቱ 3ዐ ሚልዮን ነዉ

የሚዲያ ተቋም በዜና እወጃ ሰአቱ ከዜናም በመሪ አንቀፁ/on The lead/ ይህ ከላይ የተጠቀሰው ጩኸት መጮኸ አልነበረበትም፡፡ከነበረበት ግን የሚዲያ ተቋም ሳይሆን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ክፍል መጮኸ ነበረበት ፡፡ ለምን ? ይህ አዘጋገብ እና መረጃ አሰጣጥ የክፍሉ ሙያ ስለሆነ፡፡
ከጋዜጠኛ የምንጠብቀው ግን በመሪ አንቀፁ በነገረን ስታትስቲካዊ መረጃዎች መሰረት አሻግሮ የተመለከተውን እና የዳሰሰውን ፋይዳ መሆን ነበረበት ፡፡
በዚህ መርህ መሰረት የዜናውን መሪ አንቀፅ /lead/ በምሳሌ በማስደገፍ እንዲህ መሆን ነበረበት የሚል ለሚያቀርቡ እና በውይይት እንማማርበት ዘንድ እንቀጥል ፡-


Reviewed on 2017-03-29 04:43:06
helpful?Thanks Com Hahu

Share this on social Media:

sharp pencil
sharp pencil
Level 1 reviewer
number of reviews(3)
number of helpful votes(3)

member since: 25-03-2017
LET ME SHARE YOU
FIRST I TAKE THE FOLLOWING NEWS STORY LEAD TO MY STUDENTS.

“የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ኘሮጀክት ግንባታ 9ዐ % መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት አስታወቀ፡፡ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም የዲፖው የማከማቸት ዓቅሙን በ3ዐ ሚሊዮን ሊትር ያሳድጋል፡፡”
ኢቢሲ 13 / 07 / 2009
የ2፡ዐዐ ቢዝነስ ዘገባ በቴሌቪዥን
AFTER HAVING HOT PLATE OF DISCUSSION IN THE JOURNALISM CLASS WITH MY STUDENTS I HAVE COLLECTED THE FOLLOWING LEADS FOR THE ABOVE MENTIONED NEWS STORY.PLEASE LET US MAKE THEM PART OF THE DISCUSSION AND SHARE US YOUR EXPERIENCE TO HELP MY STUDENTS @ COMMUNICATION HAHU.
1/
የአለም ኢነርጅ ኤጀንሲ ካስቀመጠው መለኪያ መስፈርት ሲነፃፀር የተጣራ መጠባበቂያ ነዳጅ የማከማቸት
ዓቅሟ 5ዐ መቶኛ የነበራት በ——— መቶኛ (3ዐ ሚሊዮን ሊትር የተባለው አዲስ የማከማቸት
ዓቅም በባለሙያ አስልቶ) እያሻሻለች ነው፡፡ ይህ ዓቅም የተፈጠረው የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ግንባታ
መጠናቀቅን ተከትሎ ነው፡፡ sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Znash Zeferu
2/
የአንድ አገር መጠባበቂያ ነዳጅ ለ9ዐ ቀናት የማከማቸት ዓቅም ላይ መድረስ የአስተማማኝ ብቃት መስፈርት
ቢሆንም ፣ እስካአሁን ለ45 ቀናት ብቻ የነበረው የኢትዮጵያ የማከማቸት ዓቅም ወደ —ቀናት (3ዐ ሚሊዮን
ሊትር በባለሙያ አስልቶ)እያሻሻለች ነው፡፡ ይህ የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ
የሚፈጠር ዓቅም ነው፡፡ sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Leadya mebrahtu
3/
እንደ የአለም ኢነርጅ ኤጀንሲ የአስተማማኝ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት መጠባበቂያ ነዳጅ ለ9ዐ ቀናት የማከማቸት ዓቅም ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያ———- (3ዐ ሚሊዮን ሊትር የተባለው በባለሙያ አስልቶ) መቶኛ ብቻ እንደቀራት ተገለፀ:ይህ የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ የሚፈጠር ዓቅም ነው፡፡ : sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Eden T.
4/
ኢትዮጵያ የአስተማማኝ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት በሆነው መጠባበቂያ ነዳጅ ለ9ዐ ቀናት በማከማቸት ዓቅም —-ደረጃ (3ዐ ሚሊዮንሊትር የተባለው በባለሙያ አስልቶ) በማሻሻል ከዓለም ልትሆን ነው sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Znash Zeferu
የ አለም አስተማማኝ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት ወደ ሆነው መጠባበቂያ ነዳጅ ለ9ዐ ቀናት የማከማቸት ዓቅም ለመድረስ ኢትዮጵያ———መቶኛ ብቻ እንደቀራት ተገለፀ sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Zerihun B
5/
ኢትዮጵያ የአስተማማኝ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት በሆነው መጠባበቂያ ነዳጅ ለ9ዐ ቀናት በማከማቸት ዓቅም —-ደረጃዎች በማሻሻል ከዓለም ደረጃ (3ዐ ሚሊዮን ሊትር በባለሙያ አስልቶ) —– ልትይዝ ነው፡፡ይህ የአዋሽ ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ የሚፈጠር የደረጃ ለውጥ ነው፡፡ ነው፡፡ sample news story lead contributed (@ journalism class discussion) by Rbka H.

helpful?Thanks sharp pencil

Asmelash
Asmelash
Level 1 reviewer
number of reviews(3)
number of helpful votes(3)

member since: 24-12-2015
I have seen a right review @ the right place which is written by Mr. Sharp Pencil @ the front page of communication hahu.As to me I prefer to quote it here.Please read the following.
የዜና መሪ አንቀፅ / The Lead/ is the remote control
በኮሚዩኒኬሽን ሀሁ የማህበረሰብ ትስስር ገፅ የኢቢሲ ዜናን በተመለከተ ፖስት ከተደረጉ ዳሰሳዎች አራቱን አነበብኩኝ
እያንዳንዱ ዳሰሳ በቀረበበት ርዕስ ሳስቀመጣቸው፡-
1. የዜናው መሪ አንቀፅ የሪፖርተሩን ጥረት አያመለክትም
2. የይድረስ ይድረስ ዘገባ እናስወግድ
3. የኣርታኢዎች ድጋፍ እና ግብአት አሰጣጡ የት አለ?
ከሶስቱም ሙያዊ የዜና ዳሰሳዎች / News review/ መረዳት የቻልኩት የዜና መሪ አንቀፅ አፃፃፍ / The Lead/ ግልፅ የዕውቀት፣ ልምድ እና ሙያዊ ክህሎት ክፍተት መኖሩን ነው፡፡
ይህ እንዲሻሻል ከሚፈልጉት ወገኖች አንዱ ነኝ፡፡ በመሆኑም የዜና መሪ አንቀፅ / The Lead/ ተኮር ሙያዊ ምክረሓሳብ የማጣቀሻ ፅሁፍ በማስደገፍ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
የዜና መሪ አንቀፅ /The Lead/ which is the opening sentence of a news story, is the most crucial element of any report.
In a matter of seconds, the viewer /or, the listener/ makes a decision whether to listen to the story actively or to merely “tune out” until something more interesting comes along. Even worse, the audience may simply move to another station with a more compelling story.
However, the vital part of the story which passes by in less than 5 0r 6 seconds, is the most difficult to write. It must set the tone for what follows, provide enough information to intrigue the audience, & offer enough news so it simply doesn’t burn away precious seconds.
‘’your greatest competition is the remote control’’ ……Don Hewitt,60 minutes.

helpful?Thanks Asmelash